መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የውጪ ኦዲተር የሥራ ጨረታ
መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቀልጣፋ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት ለመስጠት በቅርብ ጊዜ የፋይናንስ ዘርፉን የተቀላቀለ ተቋም ሲሆን፤ፍላጎት ያላቸውን የውጪ አዲት ድርጅቶች ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 (ሶስት) ተከታታይ የበጀት ዓመታት የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ ኦዲት እንዲያደርጉ ይጋብዛል:: በመሆኑም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል::
1.የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የቫት ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
2.በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ፈቃድ የተሰጠውና የታደሰ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
3.የኦዲት ስራ ለመስራት የሚያስችል ሀጋዊ ፈቃድ ያለው፣
4.በሥራው ላይ በተለይም የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ኦዲት በማድረግ በቂ ልምድ ያለው፤
5.የአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት የተከተለ ሂሳብ ኦዲት ያደረገና ልምድ ማቅረብ የሚችል፤
7.የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ከ2017-2019 ዓ.ም ድረስ ያለው የሶስቱንም ዓመት ያካተተ መሆን ይኖርበታል::
8.መባዕ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዋናው መስሪያ ቤታችን አራትኪሎ ቅድሥት ሥላሴ ዩንቨርሲቲ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2-13 በሥራ ስዓት በአካል በመቅረብ የሚሰሩበትን ዝርዝር ማብራሪያውንና ዋጋ (Technical and Financial Proposal) ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን TOR እና የጨረታ ሰነድ በተጠቀሱ ቀናት ዋናው ቢሮ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ ۸۸۸ ०८५ ۸۸h TC:- 251-928-010-203 0 251-929-010-203
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia