የሂሳብ ስራ እና ኦዲት የጨረታ ማስታወቂያ
ኢ ሜክ ኢንጂነሪንግ እና አግሮ ኢንዱስትሪ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ የ2016 በጀት ዓመት የሂሳብ ስራ እና ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1.ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ ኦዲት ቢሮ የሙያ ፈቃድ ያገኘ/ያገኘች እና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
2.በሀገሪቱ ህግ መሰረት የኦዲት ስራ ለማከናወን የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
3.የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ/ች
4.የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው/ያላት
5.ተጫራቾች የአገልግሎት ክፍያ የዋጋ ዝርዝር ጠቅላላ ዋጋቸውን ታክስን ጨምሮ እና ስራውን ስርተው የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ማለትም የሂሳብ ምርመራውን አጠናቀው ሪፖርት የሚያስረክቡበትን ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሰውን ማስረጃዎች በዝርዝር እንዲያቀርቡ ይጠበቃል::
የጨረታ ማቅረቢያ ጊዜና ቦታ
ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ ስነዱን የማይመለስ 300.00ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ::
ተጫራቾች ፕሮፖዛላቸውን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ14 የስራ ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: አድራሻ አዲስ አበባ፣ በቅሎ ቤት ከኢትዮጵያ ሆቴል የቀድሞው ግሎባል ሆቴል ከፍ ብሎ የቀድሞ የገቢዎች ቢሮ አጠገብ
ለተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተቀመጠው ስልክ ቁጥር ይደውሉ፤ +251-11470-1522 /+251-114-701339
ኢ ሜክ ኢንጂነሪንግ እና አግሮ ኢንዱስትሪ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia