የኪራይ ቤት የጨረታ ማስታወቂያ
የልደታ ካቶሊክ ካቴድራል ት/ቤት በቅጥር ግቢው ውስጥ ያስገነባውን G+4 ህንጻ ላይ ሚገኙ የተለያየ የስፋት መጠን ያላቸውን ለቢሮ እና ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎች በዝግ ጨረታ ለባንክ፤ ለኢሹራንስ፤ ለጽሕፈት መሳርያ መሸጫ፤ ለኤሌክትሮኒክክ፤ ለቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች ወ.ዘ.ተ ለማከራየት ይፈልጋል:: የሚከራዩት ክፍሎች ከትምህርት ቤቱ የትምህርት ስራ ጋር ሊሄዱ የማይችሉትን እንደ ምግብ ቤት፤ ካፌ፤ ውበት ስራ፤ ሙዚቃ ቤት እና ለመሳሰሉት ስራዎች የማይከራይ ሲሆን ከላይ ለተዘረዘሩት ስራዎች ለመከራየት ፍላጎት ያላቸው በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የተ.እ.ታ (at) ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 5 ቀናት የጨረታ መወዳደሪያ ዶክመንት ከትምህርት ቤቱ ቢሮ ቁጥር 8 በስራ ሰዓት ከጧቱ 3፡00 ጀምሮ -እስከ 7፡00 ድረስ በመግዛት የሚወዳደርበትን የኪራይ ዋጋ በካሬ ሜትር የተ.እ.ታ ጨምሮ እስከ መስከረም 29 2016 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ቤቱ ቢሮ ቁጥር 8 በሰም በታሸገ ኢንቮሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል:: ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ልደታ ካቶሊክ ካቴድራል ት/ቤት
Addis Ababa, Ethiopia