የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EPL/001/27/04/17
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ. የተቋሙን የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ እና የሥራ ክፍሎች መመሪያ ለማስራት ግልጽ ጨረታ አውጥቶ በአማካሪ ድርጅቶች ማስጠናት ይፈልጋል::
በመሆኑም በጨረታው ሊሳተፉ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራጮች፣ ከጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም አስከ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ፣ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጽ/ቤት ጎተራ ወንጌላዊት ህንጻ አካባቢ፣ ሜይስዊ ህንጻ 5ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 502 ላይ፤ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ድረስ የማይመለስ 500 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
ጨረታው ረቡዕ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ፣ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: የጨረታ ተሳታፊዎች የሚከተሉትን ሕጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦
➢ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
➢ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት፣
➢ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣
➢ ከመንግስት ግዥዎች ኤጄንሲ በጨረታ መወዳደር የሚችል መሆኑ የሚገልጽ ምስክር ወረቀት ማሟላት የሚችል::
❖ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር በሚያስኬደው መንገድ ከወንጌላዊት ሕንጻ 50 ሜትር ከፍ ብሎ፣
የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤ/ክርስቲያን ህንጻ ፊት-ለፊት፣ ሜይስዊ ህንፃ ላይ 5ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 502 ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-
0918 86 86 86 መደወል ይችላሉ::
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia