በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ኢሰመጉ ቦሌ ቡልቡላ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ግራውንድ ላይ አስፖልት ዳር ስፋት 115.81 ካሬ ለተለያየ አገልግሎት የሚውል ለባንክ፣ ለሱፐር ማርኬት፤ ለፋርማሲ እና ለተለያዩ የንግድ አገልግሎት የሚውል የንግድ ሱቅ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል::
ስለሆነም ፍላጐት ያለው ግለሰብም ይሁን ድርጅት የጨረታ ሰነዱን ብር 400.00 (100) ከድርጅቱ መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት የሚገኘው የወጋገን ዋና መ/ቤት ጐን ሳህለ ስላሴ ህንጻ 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19 የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ:: የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን ማስገባት የሚቻለው 7 (በሰባቱ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን በሰባተኛው ቀን ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም 9:00 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ሲሆን በዚሁ ቀን ከሰዓት 9፡20 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል::
ጨረታውን የሚያሸንፈው ድርጅት ወይም ግለሰብ ውጤቱ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 3 የሥራ ቀናት ውስጥ የንግድ ቤቱን ኪራይ ዋጋ ከፍለው ለመከራየት ውል መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡ ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ኢሰመጉ
ስልክ ቁጥር +251 186 68 57 05 +251 901 59 43 27
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia