የጨረታ ማስታወቂያ ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ
Abay Insurance S.C
1. ዓባይ ኢንሹራንስ ኢማ የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረክባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
2. ተሽከርካሪዎቹን ፤ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት ቅሪቶችን ለመግዛት በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ሁሉ ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በቅድሚያ ክፍሎ ከዋናው መ/ቤት በመግዛት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አሃናማርያም አደባባይወደ ቃሊቲ በሚወስደው ቀለበት መንገድ 800 ሜትር ወረድ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ሪክቨሪ በመቅረብ ከየካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በስራ ሰዓት ብቻ በመምጣት ማየት ይቻላል ::
3. ተጫራቾች ተሽከርካሪውን ወይም እቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከየካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጧቱ 3.00 ሰዓት ድረስ አትላስ አካባቢ በሚገኘው የአባይ ኢንሹራንስ ኤማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የሚጫረቱበትን ዕቃ ኮድ በጨረታው ፖስታ ላይ በመጻፍ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ::
4. ተጫራቾች ዝቅተኛ ማስያዣ ብር 1,000.00 ሆኖ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 15% በ CPO የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ሶስት የስራ ቀናት በኃላ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል::
5. የጨረታው አሸናፊዎች የተሸከርካሪዎችንም ሆነ የዕቃዎችን ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል ተሽከርካሪዎችንና እታዎችን በ10 ቀናት ውስጥ ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል::
6. ተሽከርካሪዎች በጨረታ እስከተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ቢኖር የሻጭ ኃላፊነት ይሆናል:: ተሽከርካሪዎቹ ከተሸጡ በኋላ የሚፈለግ ግብርና ታክስ፤ ስም ማዛወርያ እንዲሁም ሌላ ክፍያ ቢኖር የገዢው ኃላፊነት ይሆናል::
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀ ቅፅ መሰረት የሚገቡትን ዕቃ ዋጋና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን በግልጽ ሁኔታ በተናጥል ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
8. ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪዎችን ኩባንያው ለገዢዎች የሚያስረክበው ገዢዎች በቅድሚያ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚወስነውን ቀረጥና ታክስ ክፍያ ከፍለው ተገቢውን ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ይሆናል::
9. አሸናፊ ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹንም ሆነ ሌሎች ዕቃዎችን ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ ሳይነጣጥሉ በጠቅላላ በአንድ ጊዜ ማንሳት ይኖርባቸዋል::
10.ጨረታው ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል:: ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ 0115 15 45 07 : 0115 51 08 17 I 0115 - 53 53 001 0913 57 01 55 ደውለው መረጃ ማግኘትይ ችላሉ::
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia