ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የጨረታ ማስታወቂያ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
BERHANENA SELAM PRINTING ENTERPRISE
የጨረታ ማስታወቂያ
ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ለኅትመት አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫዎች፣ የተለያየ መጠን እና ብዛት ያላቸው ወረቀቶችና የኅትመት ግብዓቶች ማለትም Leather Board የተለያየ ከለር ማኒላዎች፣ Web Process Ink Offset Process ink, Wire Balacron, Tella, Glue, የማኅተም መርገጫ እንጨት Cliché Mterials, Negative Plate, Termal Plate, Violet Plate, Positive Plate Developer Chemical, Violet CTP Developer Chemical, Gum Thermal Chemical, Film Developer CEG 101P Powder, Positive Plate Corrector 250 cc, Film Image Setting 66CMX60M, fixer
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፣
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ በዋናው ቅጥር ግቢ በሚገኘው የማርኬቲንግ ሽያጭ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመምጣት የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200 በመክፈል መግዛትና ንብረቶቹንም ማየት ይቻላል::
3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
4. ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ በሰም በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፣ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል::
5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia