የጨረታ ማስታወቂያ የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር የጭነት መኪና በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ፣ በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት ቡታጅራ ከተማ 01 ቀበሌ ቅ.ማሪያም ቤተክርስትያን አጠገብ ወይም አ/አበባ ፒያሳ የሚገኘው ጉልባማ ጽ/ቤት መግዛት ይቻላሉ::
2. ተጫራቾች ብር 100,000 (መቶሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
3. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀነ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
4. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
5. የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 046-115-03-12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia