የጨረታ ማስታወቂያ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCDE 018/2017
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ተሸከርካሪዎች/መኪናዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል::
በዚህም መሰረት፡-
1. ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደስ ታክስ ክሊራንስ ፤በዘርፉ የታደስ የንግድ ፈቃድ፣የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋመበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል::
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከተገለፀው ቀንና ሰዓት በፊት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
5. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
6. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል::
7. የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ(CPO) ብር 25,000.00(ሃያ አምስት ሺህ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
8. ጨረታው ከጥር 04 ቀን 2017 ዓ/ም እስከ ጥር 19 ቀን 2017 ዓ/ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጭን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥ ዴስክ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም::
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
011 896 06 33 /011 896 06 23
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia