የጨረታ ማስታወቂያ ኢሳት ነጻ የሕዝብ ሚዲያ
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢሳት ነጻ የሕዝብ ሚዲያ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ 3 (ሶስት) ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልዕ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ስለሆነም ..
ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪው በሚገኝበት ባምቢስ አካባቢ አፈወርቅ ሕንጻ ዐሥረኛ ፎቅ በሚገኘው የኢሳት ነጻ የሕዝብ ሚዲያ ቀርበው በማናገር ከየካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተሽከርካሪዎችን በማንኛውም የሥራ ሰዓት መመልከት ይችላል፤
1. ተጫራቾች ከየካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከላይበተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ:: ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያየዘው የተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ::
2. ተጫራቾች በወሰዱት ስነድ ላይ የሚፈልጉትን ተሽከርካሪ መርጠውና የሚገዙበትን ዋጋ ሞልተው በአሃዝና በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሽገ ኤንቬሎፕ/ፖስታ፤ ባምቢስ አካባቢ በሚገኘው አፈወርቅ ህንጻ 10ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚያስገቡበት ወቅት የተሽከርካሪውን መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አስርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል:: የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፤
4. ጨረታው ከየካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና ከጥዋቱ 4፡05 ይዘጋል፡፡ በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙብት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል:: በወቅቱም አሸናፊዎች ይገለጻሉ::
5. ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሽናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል::
6. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል::
7. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኢሳት ነጻ የሕዝብ ሚዲያ
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia