ያገለገሉ ንብረቶች የጨረታ ማስታወቂያ
ናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ያገለገሉ የብረት በርሜሎች፡ ያገለገለ የከባድ እና የቀላል መኪና ጎማዎች፡ አሮጌ የመኪና ባትሪዎች ያገለገለ ፊልትሮዎች እና ዳፕራተር፣ የተለያየ መጠን ያላቸዉ ፓይፕ፡ የተቃጠለ ዘይት፡ ፍሌክስብል ሆዝ አሮጌ ከለመነዳሪ እና ፍላፕ፣ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም ማንኛዉም የታደሰ ንግድ ፍቃድና የግብር ክፍይ መለያ ቁጥር ያለዉ ተጫራች ከ04/13/2016 ዓ.ም ጀምሮ ቃሊቲ ፋብሪካችን ድረስ ቀርቦ ማየት ይችላል::
1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200.00 ብር በመክፈል ከ04/13/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 13/01/2017 ዓ.ም በስራ ሰዓት በዋና ቢሮ ባምቢስ ምንትዋብ ህንፃ ገባ ብሎ የሚገኝ መስሪያ ቤት ከግዢና አቅርቦት ክፍል መግዛት ይችላሉ::
2. ጨረታው በቀን 13/01/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 8፡ 30 ሰዓት ላይ የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል::
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ወይም በባንክ ጋራንቲ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር በታሽገ ፖስታ ከፋይናንሻል ዶክመንት ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል::
4. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ዉል ተፈራርሞ ክምችት ላይ ያለዉን ንብረት ማንሳት አለባቸዉ ::
5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ: ባምቢስ ፤ ምንትዋብ ህንፃ ገባ ብሎ ስልክ ቁጥር 0930329140/0930329141
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia