የጨረታ ማስታወቂያ ግዮን ጋዝ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዮን ጋዝ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር አገልግሎት የሰጡ ከባድ መኪኖች/የጭነት/ እና አነስተኛ ተሽከርካሪዎች /አውቶሞቢሎች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::ስለሆነም፡-
1. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ማግኘት ይችላል::
2. ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡትን ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ወይም በሲፒኦ በማስያዝ ማስረጃውን ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ከሞሉ በኋላ በጎተራ ዋናው መ/ቤት ሀብት አስተዳደርና ፋሲሊቲ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባ አለባቸው::
4. የጨረታው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ ጋዜጣ በወጣ በ 10ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
5. ተጫራቾች ተሽከርካራዎቹን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡30 ዱከም የሚገኘው ጊዮን ጋዝ ቅጥር ግቢ እና ጎተራ ዋናው መስሪያ ቤት ማሳለጫ ከቶታል ዲፖ ጀርባ በሚገኘው የዋና መ/ቤቱ ግቢ በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ::
6. በቂ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል::
7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ጎተራ መሳለጫ ወንጌላዊት ሀንፃ ገባ ብሎ ምስራቅ የምግብ ማቀነባበሪያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ግቢ ውስጥ እንገኛለን::
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር፡-0114162827/0114165614/6317/ E-Mail:info@ghions.com.et Website:www.ghions.com.et
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia