የጨረታ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን /ኢሠማኮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን /ኢሠማኮ/ በዋናው መስሪያ ቤት ትንሹ ሕንጻ ላይ ሁለተኛ ወለል፤ ሶስተኛ ወለል እና አራተኛ ወለል የሚገኙ ክፍሎችን አሁን ባሉበት ሁኔታ ለቢሮ አገልግሎት ወይም በተከራይ ሙሉ ወጪ ክፍሎችን በመቀላቀል ለተለያዩ የንግድ ሥራዎች ለመጠቀም ለሚፈልጉ ተከራዮች በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል:: በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣
1. የጨረታው ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ኢሠማኮ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 212 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውስድ ትችላላችሁ::
2. የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Boned/ የሽያጭ ሰነድ ላይ በዝርዝር በተገለጸው መሠረት መፈጸም አለባችሁ፡
3. የጨረታ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ Nav ሳይጨምር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ Nav ጨምሮ መሆኑን በግልጽ ተለይቶ መገለጽ አለበት::
4. የጨረታው አሸናፊ የሶስት ወራት ኪራይ ክፍያ የተጨማሪ እሴት ታክስ Nat/ጨምሮ በቅድሚያ የመክፈል ግዴታ አለበት::
5. የጨረታው አሸናፊ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልቶ የመረከብ ግዴታ አለበት:: በተሰጠው ቀነ ገደብ ቀርቦ ለመዋዋልና ለመረከብ መቅረብ ካልቻለ ለጨረታ ማስረከቢያ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለኢሠማኮ ገቢ ይሆናል::
6. ማንኛውም ተጫራች የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል:: እንዲሁም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ ወይም ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን አለበት::
7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣ በ 11'ው ቀን ከረፋዱ ልክ በ4:00 ሠዓት ኢሠማኮ ሕንጻ 11° ፎቅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኩሎቻቸው በሚገኙበት የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሠዓት ይከፈታል::
8. በጨረታው ለመወዳደር ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 10 ተከታታይ ቀናት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ኢሠማኮ ትንሹ ህንጻ ቢሮ ቁጥር 216 በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይችላሉ::
9. ተጫራቾች ከ2" እስከ 4" ወለል ያለውን በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ::
10.ኮንፌዴሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ
ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ላይ ፍላሚንጐ ሳይደርሱ ወይም ሠላም ፓርክ አጠገብ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 011 515 79 81 / 09 11 95 87 81
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia