Tender Title
የጨረታ ማስታወቂያ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2017
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
1. የተለያዩ የቴክኒክ መገልገያ ማሽኖች Air compressor እና ሌሎች ዕቃዎች
2. የጽሕፈት መሣሪያዎች
3. የዕዳት ዕቃዎች
4. የተለያዩ የደንብ ልብሶች
5. የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች፤ባትሪዎች እና በልቦች
6. የተለያዩ የቧንቧ ዕቃዎች፣
7. የተየያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
8. የተለያዩ መጠን ያላቸው ብረታብረቶች እና ሌሎች ዕቃዎች
9. ለሕንፃ ግንባታ እና ጥገና የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎች እና የሕንፃ ቀለሞች
ማንኛውምተጫራች፡-
➢ በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ ለተጨማሪ አሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያጋግጥ የምስክር ወረቀት ፤የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
➢ ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በሥራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላል፣
➢ የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ/ ለሚጫረትበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ፣በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ በድርጅቱ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርበታል፣ የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
➢ ጨረታው መስከረም 07 ቀን 2017ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል:: በጨረታ አከፋፈት ሒደት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ የጨረታ ሒደቱን አያስተጓጉለውም::
➢ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-4-65 22 94 /0114 66 47 05 መጠየቅ ይቻላል:: የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia