የጨረታ ማስታወቂያ አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ. የግል ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ. የግል ማህበር
የጽሕፈት መገልገያ መሳሪያዎች፣ የቢሮ መገልገያ ልዩልዩ ዕቃዎች፤ የጽዳት መገልገያ ዕቃዎች እና ለሳኒቴሽን አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች፤ለIT አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች፤ ለህንፃ ጥገና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች፣ -የተለያዩ ዲያሜትር ያላቸው የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ማፅጃ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም፤
1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ሕጋዊ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ እንዲሁም በጨረታው ለመሳተፍ የሚያበቃ የዘመነ ግብር የተከፈለበት የግብር ክሊራንስ ስልጣን ካለው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት::
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በገዥ አድራሻ ማለትም አ/አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር አዲስ ኢትዮ-ቻይና መንገድ (በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ) አምባስል ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503፣ ተገኝቶ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
3. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው እ.አ.አ. ኖቬምበር 25 /2024 ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን (ለሥራ ቀን አቆጣጠር ሲባል ቅዳሜ ከጥዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ያለዉ ጊዜ የአገልግሎቱ ገዥ የሥራ ቀን ስለሆነ እንደ አንድ ሙሉ የሥራ ቀን ይቆጠራል) ጨረታው በ10ኛው ቀን ማለትም እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 05/2024 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11 ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት አዲስ አበባ ዋና መ/ቤት ማለትም አምባሰል ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ላይ የጨረታ መከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: በጨረታ መክፍት ስነ-ስርዓቱ የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታውን ዋጋ አያሳጣውም::
4. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦
ስልክ ቁጥር - 0114700349 /0114700346 ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይቻላል፤
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia