የጨረታ ማስታወቂያ አለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
Tender no:- AKGC 02/2017/LCB
አለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎች፥ ባትሪዎች ፣ ባዶ የብረት እና ፕላስቲክ በርሜሎች፣ ስክራፕ ዋየር፣ እንጨቶች እና ፕሌይውድ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡
❖ ለ2017 ዓ.ም የሥራ ዘመን የታደሰ ንግድ ፈቃድ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ከጃክሮስ ወደ የረር በሚወስደው መንገድ በአለማየሁ ህንጻ የሠው ኃይል ልማትና አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
❖ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
* ተጫራቾች ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው::
❖ ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የካቲት 06 ቀን 2017ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ሲሆን ፣ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የካቲት 06 ቀን 2017 ዓ.ም. ከሰዓት 9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአለማየሁ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ዋና መ/ቤት ይከፈታል::
❖ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ አለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት ስ.ቁ. ሞባይል - 0116-47-77-95
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia