የጨረታ ማስታወቂያ ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ
የጨረታ ማስታወቂያ
No TC SD/52/24
ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ጉዳት ደርሶባቸው ለደንበኞች ተገቢውን ካሣ ከከፈለ በኋላ የተረከባቸውን ቀረጥ የተከፈለባቸውና ያልተከፈለባቸው ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም ኩባንያው ሲገለገልባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች እና ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
ተጫራቾች በኩባንያው የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር መመሪያና ዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ከኩባንያው የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማከማቻ- ቃሊቲ/ Wreck Yard/ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ ከፍለው በመውሰድ ይህ ማስታዎቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የሚዎዳደሩባቸውን ንብረቶች ዝርዝር በመግለጽ እስከ ነሀሴ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጧት 4፡00 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ፖስታ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ሚኪሊላንድ መንገድ በሚገኘው ፕሮቴክሽን ሀውስ በምድር ቤት ዋናው መግቢያ ላይ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የሚገዙትን ዕቃ ዋጋ ከነቫቱ በመግለጽ በኩባንያው መነሻ ዋጋ ላይ 10% የጨረታ ዋስትና ለኩባንያው በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) አሠርተው ከጨረታው ሠነድ ጋር ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል::
ጨረታው በዕለቱ ነሀሴ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ከጧቱ 4፡30 ሰዓት በኩባንያው የሠራተኞች ክበብ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫራታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ.
የስልክ ቁጥር 011-6-626667
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia