የጨረታ ማስታወቂያ ለሽንኩርት ዘር ግዥ የዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ
ዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ትርፋማ ያልሆነ በሲቪል ማህበር ድርጅት ኤጀንሲ እ.ኤ.አ. 2004 ተመዝግቦ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እያደረገ ያለ የውጭ ድርጅት ነው :: በአሁኑ ጊዜ ድርጅቱ ለሚሰራዉ የህብረተሰብ አቀፍ ፕሮጀክቶች ግብዓት የሚሆን የሽንኩርት ዘር የሚያቀርቡ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ስለፈለገ በሠንጠረዡ ዉስጥ በቀረበዉ መሰረት ማቅረብ የምትችሉ አቅራቢዎችን ማወዳደር ይፈልጋል:: የሽንኩርት ዘር ዓይነትና ዝርዝር ከዚህ በታች በሠንጠረዡ ዉስጥ ተዘርዝረዋል::
የዘር ዓይነት :- ቀይ ሽንኩርት (Bombe Red)
ብዛት :- 210 k.g
ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛዉም ፍላጎት ያለው ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ይጠበቅበታል::::
ማንኛዉም ፍላጎት ያላቸውና ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ በአካል በመቅረብ ማስገባት አለበት:: ተወዳዳሪ ድርጅቶች በተጠየቀዉ መስፈርት መስረት በዋጋ መሙያ ላይ የአንድ ኪ/ግ ዋጋ ብቻ በመሙላት ማቅረብ ትችላላቹሁ: ድርጅቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
ማሳሰቢያ የጨረታዉ አሸናፊ የተጠቀሰዉን የሽንኩርት ዘር ውል 879 03 ቀን ዉስጥ ማቅረብ ይኖርበታል
አድራሻ፡ ዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ጽ/ቤት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ቤት ቁጥር 765/04 አዲስ አበባ፣ ምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፍ ብሎ የሚገኝ ሲሆን ተጫራቾች በስm መረጃ በስልክ ቁጥር 0111 267151/267950 +251913258163
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia