የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ
Ref No:- ERCS/SVC/005/25
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፈው ድርጅት ጋር እንደ ሁኔታው የሚታደስ ለ1 (አንድ) ዓመት የደረት ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈራረም ይፈልጋል፡፡
በመሆነም ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚገልፅ የንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ስርተፍኬት፣ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የጭነት አገልግሎት የደረጃ ብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፍኬት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
2. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000000950487 ብር 300 (ሶስት መቶ) ገቢ በማድረግ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ስዓት ስታዲዮም አካባቢ ከሚገኘው ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋናው መስሪያ ቤት የስብዓዊ ግብአት አቅርቦት መምሪያ ከግዥ ዋና ክፍል የጨረታ ስነዱን በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የፋይናንሻል ስነድ ኦርጅናል እና ኮፒ የቴክኒክ ሰነድ ኦርጅናል በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያ በተለያዩ ኢንቨሎፖች በማድረግ አራቱንም ኢንቨሎፖች በአንድ ላይ በማሽን ከዚህ በታች በተጠቀሰው የማህበሩ አድራሻ "የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ' ጨረታ የሚል በመጻፍ የመጫረቻ ስነዳቸውን ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ወይም ቀደም ብሎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) በሲፒኦ ብቻ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የትራንስፖርት አገልግሎት ዋጋ የአንድ ኩንታል በኪሎ ሜትር ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
6. ጨረታው ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀነ- በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: በመሆነም ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሱት ቀናት በስራ ሰዓት ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ 25 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው::
7. ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ብሔራዊ ጽ/ቤት
0115180175
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia