የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር
Construction Contractors Association of Ethiopia
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር በዓይነቱ ለየት ያለ የኮንስትራክሽን ኤግዝቢሽን ከጥር 15 - 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ ኤግዝቢሽን ማዕከል ለማካሄድ ዕቅድ በመያዝ ይህንኑ ኤግዝቢሽን የኹነት ዝግጅት (Event Organization) የማዘጋጀት ፈቃድና ልምድ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ በመቅጠር ለማሠራት ይፈልጋል::
ስለሆነም ይሀንን ዝግጅት ለማዘጋጀት ፍላጎቱ፣ የንግድ ፈቃዱና ልምዱ ያላችሁ ድርጅቶች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ የዕሁድ ጷግሜን 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በማኅበሩ ፅ/ቤት በመገኘትና ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍሎ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን:: ማኅበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማሕበር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 1፣ ኃይለገብርኤል ህንፃ፣ 3ኛ ወለል፣ ቢሮ ቁጥር 305 0 303:
+251 11 5524723 .4.Ф. 22171 (1000)
ኢሜይል ccae2002@gmail.com
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia