የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል ማሰልጠኛ ተቋም
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል የመጀመረያ ሕክምና መስጫ ሳጥን (First Aid Kit) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-
1. ህጋዊ የታደሰ የስራ ፈቃድ፣የግብር ከፋይ ስርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
2. ተቋሙ ድረስ በመምጣት በሳጥኑ ውስጥ የሚካተቱን እና የሳጥኑን ልኬትና አይነት የያዘ ዶክመንት በብር 200.00 ገዝቶ በመውሰድ ዋጋ መስጠት፣
3. በጨረታው ለመወዳደር ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. አዘጋጅቶ ማስያዝ ይኖርበታል፣
4. የጨረታ ሰነዱን በፖስታ አሽጎ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በግንባር ቀርቦ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት እሁድን ባይጨምር ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አደይ አበባ ገባ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
5. የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፣
6. ጨረታው ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበ የሚከፈት ይሆናል፣
7. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አለሟሟላት ከጨረታው ውጭ ያስደርጋል::
8. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ 0114407460 /011420235 ላይ መደወል ይቻላል::
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia