ኮከብ ዱቄት ወኪል አከፋፋይ መሆን ለሚፈልጉ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
ተወዳጅ ምርታችን የሆነውን ኮከብ ዱቄት ወኪል አከፋፋይ መሆን ለሚፈልጉ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ኮከብ ዱቄትና ፓስታ ፋብሪካ ላለፉት 20 ዓመታት በሀዋሳና አዲስ አበባ ከተሞች ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የስንዴ ዱቄት በቀን 1160 ቶን በላይ በማምረትና በማሰራጨት በማህበረሰባችን ዘንድ አይረሴነትን ከመፍጠሩም በላይ እጅግ ተወዳጅና ተመራጭ የስንዴ ዱቄት ነው :: በመሆኑም የማህበረሰባችንን ፍላጎት ለማስደሰት ያስችለን ዘንድ ምርታችንን ለተጠቃሚ በቀጥታ ለማድረስ ወኪል አከፋፋዮችን ማሳታፍ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል:: በዚህ መሰረት ብቁ አከፋፋዮች በሁለቱም ከተሞች የምናመርተውን በሁሉም የሀገራችን የክልልና ዞን ከተሞች ማከፋፈል የሚችሉና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል::
1. ደረጃውን የጠበቀ መጋዘን ያለው::
2. ለማከፋፈያ ምቹ የሆኑ መኪኖች ያሉት::
3. በቂ የካፒታል መጠን ያለው ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ የሚችል::
4. ስራውን በትጋት መስራት የሚችል::
5. በተሰጠው የማከፋፈያ ክልል ውስጥ የድርጅቱን ምርት ለሁሉም ደንበኞች ማከፋፋል የሚችል::
6. -ህጋዊ ንግድ ፍቃድና የኢት/ያ የግብር ህግ በሚጠይቀው መሰረት የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ያለው ህጋዊ ደረሰኝ መስጠት የሚችል::
7. የድርጅቱን ምርት ማከፋፈል ብቸኛ የገቢ ምንጭ አድርጎ መስራት ለሚፈልጉ ብቁ ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ የምንሰጥ መሆኑን በአክብሮት
ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾች አዲስ አበባ ሳሪስ 58 ዳማ ሆቴል በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ማመልከት ትችላላቹ::
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር +251-9-38-09-30-81 +251-9-33 74 00 74 ሀብታሙ ብለው ይደውሉ:: 46
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia