ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ የጨረታ ማስታወቂያ
CN/DE/01/16
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በድርጅታችን አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የተለያዩ ያገለገሉ ብረታ ብረቶች እና ቆርቆሮዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ሕንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 300.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (mዋት 2:00-6:00 እንዲሁም ከሠዓት 7:00-11:00) ማግኘት ይቻላል:: ተጫራቾች የዕቃዎቹን ሁኔታ ቀጠሮ በማስያዝ ገርጂ በሚገኘው የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት እንዲሁም ቃሊቲ በሚገኘው ጃቲ የዕቃ ግምጃ ቤት በአካል በመገኘት መመልከት ይቻላል::
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመስብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ስልክ ቁጥር 011-555 19 11 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia