በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ
ቁጥር HP/0006/16
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አግሮ ክላስተር ስር የሚተዳደረው ድርጅታችን ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ.የተ.የግል ማኅበር በስሩ ከሚያስተዳድራቸው በጅማ ዋናው ቢሮ እና በስምንት እርሻዎች የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ውድቅዳቂ ብረታብረቶች፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ባትሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን በሟሟላት መጫረት ይችላሉ::
1. ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ ሰነዱ ጋር በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለበት::
2. ያገለገሉ ዕቃዎቹን ዝርዝር የያዘውን በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 01 ዘውትር በሥራ ቀንና ሰዓት እስከ ጳጉሜን 01 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
3. የመጫረቻ ሰነዶች ማንኛውም ለውጥም ሆነ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም
4. ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 50.000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሆ'ራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር /HORIZON PLANTATIONS PLC/ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ. /CPO/ ብቻ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው::
5. የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል::
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
7. ጨረታው ጳጉሜን 01 ቀን 2016 ዓ.ም. ክቀነ- 8፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911899634 /0912171333 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ - አዲስ አበባ መካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን እለፍ ብሎ በሚገኘው ኩዊንስ ስፐር ማርኬት ጎን:: ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማህበር
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia