በድጋሚ የወጣ የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ
ጂ ኤስ ቤት ግንባታና ኪራይ አክሲዮን ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 1 በመርካቶ አካባቢ የ 2B+SB+G+12 ወለል ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንፃ በመገንባት ላይ ያለ አክሲዮን ማህበር ነው::
የአክሲዮን ማህበሩ የሚያስገነባው ህንፃ የ 2B+SB+G+3 /3ኛ ወለል ላይ/ ደርሶል::
የአክሲዮን ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤዎች ለባለአክሲዮኖች ተደልድለው ክፍያ በወቅቱ ያልተፈፀሙባቸውን አክሲዮኖች ለባለአክሲዮኖችም ሆነ ለውጭ ፈላጊዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: በዚህም መሰረት ዝርዝር የጨረታውን ሁኔታ እና ሂደት በተመለከተ ተጫራጮች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፍል የጨረታ ሰነዱን ከማህበሩ ፅ/ቤት መውሰድ ይችላሉ:: .
ጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚመልሱበት ጊዜ ያስገቡትን የአክሲዮኖች ጠቅላላ ዋጋ 5 ፐርሰንት ሲፒኦ በማህበሩ ስም አሰርተው አያይዘው በታሽገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተጫራጮች የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ::
ጨረታው ሀሙስ ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ተዘግቶ በማግስቱ አርብ ህዳር 27 ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጨራቾች ባሉበት የሚከፈት ይሆናል::
አድራሻ፡- መርካቶ አሜሪካን ግቢ አካባቢ አባ መላ የገበያ ማዕከል እየተገነባ ያለው ህንፃ ውስጥ 2ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር
0911 43 83 71/ 0911923333
ማሳሰቢያ፡- አክሲዮን ማህበሩ የተሸሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia