Site logo

Amharic Book Suggestion

መጽሐፍ ጥቆማ
የአባ ባህርይ ድርሰቶች
አባ ባሕርይ ድርሰቶች ኦሮሞዎችን ከሚመለከቱ ሌሎች ሰነዶች ጋር
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
⛵️⛵️⛵️
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ጥልቅ ምርምር አድርገው ካዘጋጇቸው መጻሕፍት መካከል አንዱ የሆነው ይህ ድንቅ ሰነድ ጥቂት ቅጅዎች አሉን።
ይኸውም ፕ/ር ታደሰ ታምራት ስለ መጽሐፉ በቀዳሚ ቃል የጻፉትን ክታብ በአጭሩ እንዲህ ይላሉ፡፡”ጌታቸው ስለ ኦሮሞዎች ታሪክ ሲጽፍ የአባ ባህርይን ጥናት ለብቻው ነጥሎ ሳይሆን ከአጼ ገላውዴዎስ ጀምሮ እስከ 20ኛው መ/ክ/ዘ መጀመሪያ ድረስ የነበሩ የነገስታት ዜና መዋዕሎችን ከሌሎች የታሪክ ድርሳናት ጋር እያዋሃደ ማቅረቡ እጹብ ድንቅ ያሰኛል፡፡

የአፄ ሱስንዮስ ዜና መዋዕል ፀሐፊ ኦሮሞው ሊቅ የአዛዥ ተክለ ሥላሴ ጢኖ፣የታወቁት ኦሮሞ ታሪክ ፀሐፊና ሠዓሊ የጎጃሙ ሊቅ የአለቃ ተክለ ኢየሱስ ዋቅጅራ፣ እንዲሁም 19ኛው መጨረሻና 20ኛው መ/ክ/ዘ መጀመሪያ ላይ የነበሩት የነ አቶ አጽሜና አለቃ ታየ የሌሎችም ድርሳናት መካተቱ ሃሳቡን ምልዑ ያደርገዋል፡፡ ስለ ኦሮሞ የተጻፉ ቀደምት ሰነዶች በጦርነትና በትግል ጊዜ በመጻፋቸው የቁጣና የዘለፋ ቃላት ይበዛባቸዋል (የአባ ባህርይን ድርሰት ማለታቸው መሰለኝ)፡፡

አቶ አጽሜና አለቃ ታየ ግን ከጊዜው በኋላ ስለተገኙ በዘመናቸው ይህንን መንፈስ ለማሻሻል ጥረት ያደርጉ እንደነበር ድርሰቶቻቸው አፍ አውጥተው ይናገራሉ፡፡ ይህንን ተገቢ እርምጃ ጌታቸው በዚህ መጽሐፍ የበለጠ አዳብሮታል ማለት ይቻላል” በማለት ሃሳባቸውን ያጋራሉ፡፡
.
——————————–
🚢
Free Delivery
መፅሐፉን ለማዘዝ

Noah book 0939115238

“ማንበብ ፋሽን ነው።”

Comments

  • No comments yet.
  • Add a comment
    Home
    Explore
    Advertise
    Leads
    Account