ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የጨረታ ማስታወቂያ
ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ.
BERHAN INSURANCE s.e
የጨረታ ማስታወቂያ
በብርሃን ኢንሹራንስ ኢማ ሲገለገልባቸው የነበሩ አደንበኞች የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ (ፕላስቲክ ነክ የሆኑና ያልሆኑ ራዲያተር፣ ኤሲ ኩለር! ገቢናዎች ባትሪ ወዘተ ) ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር መሰረት ባሉበት ሁኔታ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ከዋናው መስሪያ ቤት መግዛት ይችላሉ::
1 ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የተጎዱ ንብረቶች ማከማቻ ቦታ አታቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ቃሊቲ 40/60 ኮንደሚኒየም በኩል ገባ ብሎ በተለምዶ የቆላ ዝንብ አካባቢ (ጨራ ሰፈር) )የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ ::
2 በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት የሚፈልገውን የንብረት አይነት እና ያቀረበውን የጨረታ ዋጋ ዝርዝር በመግለፅ îየጨረታ ማስከበሪያ የንብረቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 15 በመቶ (15%) በባንክበተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ስም በማስያዝ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ በስራ ቀናት ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ዋናው መ/ቤት ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ቦሌ ወሎ ሰፈርጋራድ ሲቲ ሴንተር 7 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል በመገኘት የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ፖስታ ለሚጫረቱበት የእቃ አይነት ማስገባት የችላሉ::
3 በጨረታ ለተሸነፉ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል:: ለጨረታ አሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙት ገንዘብ ለሚገዙት የተሸከርካሪ ወይም መለዋወጫ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋርይታስብላቸዋል::
4 አሸናፊዎች በጨረታው ላሸነፉት ንብረት ቀሪውን ክፍያ እና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን አክለው በመክፈል የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ እቃዎችን መረከብ ይኖርባቸዋል:: በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ያሸነፉትን ንብረት ከፍለው ካልወሰዱ ኩባንያው ለጨረታ ያስያዙትን ሲፒኦ ገቢ አድርጎ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
5 ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልፅ ሁኔታ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ካልተገለፀ በስተቀር በቀረበው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል::
6 ተሸከርካሪዎች በጨረታ እስከተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ወይም ሌላ ክፍያ የሻጩ ሃላፊነት የሆናል::
7 አሸናፊ ተጫራቾች የገዙትን እታ ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ::
8 ጨረታው የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀነ- 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል::
9 ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-67-44-23 /46 ወይም 0114-70-40-54
መደወል ይችላሉ::
አድራሻ
ብርሃን ኢንሹራንስ ኢማ ዋናው መ/ቤት
ቦሌ ወሎ ሰፈር ጋራድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 የሰው ኃይልና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
0114674423/46
0114704054
Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 3578, Ethiopia