የመኪና ሽያጭ ውል……
የተሽከርካሪ የመኪና ሽያጭ ውል ለመፈፀም በዉል አዋዋይ ፊት ሲቀርቡ ሟሟላት ያለባቸዉ ሰነዶች
• በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የሽያጭ ውል ሰነድ(ፎርም)፤
• የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ፤
• የሻጭና የገዥ ህጋዊ መታወቂያ፤
• ሻጭ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ የመሸጥ ስልጣንን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ሰነድ፤
• ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
• የሻጭ ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
• ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የመኪና ዋጋ ግምት፤
• ለኮድ 1 እና 3 ከትራንስፖርት ባለስልጣን እና ከገቢዎች የሚሰጥ ክሊራንስ፤
• ለኮድ 1 እና 3 አስር ዓመት ቢሞላውም ከቀረጥ ነፃ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ ከቀረጥ ነፃ መብት ማስተላለፍ ባለሥልጣን የተፃፈ ደብዳቤ ወይም ይህን መነሻ በማድረግ መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠው የማረጋገጫ ሰነድ፤
• ለኮድ 5 11 እና 35 የመሳሰሉት ከሐይማኖት ተቋማት በስተቀር ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የተሰጠ የማስተላለፍ የዕውቅና (የድጋፍ) ደብዳቤ፤
• ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ የምስከር ወረቀት የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ስራ አስኪያጅነት የሚገልጽ ደብዳቤ፤
Source Samuel Girma legal service